Sunday Services: Prayer (9:00 am), Worship (10:00 am)

Men’s Ministry (የወንድሞች ኅብረት)

የወንድሞች ኅብረት መሪ ቃል፤ “ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነው እነሆም ያማረ ነው። በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ህይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።” [መዝ 133÷ 1,3]

የወንድሞች ኅብረት የአባላትን የመንፈሳዊ እድገት፤ የአእምሮ መታድስ፤ እና የአካላዊ ብቃት ለማጎልበት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችንና ትምህርቶችን ያዘጋጃል። ከግለሰብም አልፎ፤ በቤተሰብ ጉዳዮች እና በቤተክርስቲያን ደረጃም በመንፈሳዊ፤ በአዕምሮዊና በአካልዊ መስኮች ምሳሌ በመሆንና ከሌሎች ኅብረቶች ጋር በመተባበርና በመምራት ይሳተፋል።

የወንድሞች ኅብረት ተለዕኮና ቦች፡ የቤተክርስቲያኗን የኅማማተ (ኅብረት፤ ማደግ፤ ማገልገል፤ ተለዕኮ) ራዕይ መፈጸምና ማስፈጸም።

* ኅብረት ወንድሞች ኅብረትን በማድረግና በማጠንከር ፍቅርን ማሳደግ፤ እርስ በርስ መቀባበልን እና መደጋገፍን ማጎልበት፤

* ማደግ፦ ወንድሞች በጋራ በፀሎት በመሆንና ቃሉን በማጥናት እንድሁም ኅብረቱን የሚያጎለብቱ ትምህርቶችን ማዘጋጀት፤

*ማገልገል፦ እያንዳንዳችን የተሰጠንን ፀጋ በመረዳት በእግዚአብሔር መንግስት ሥራ ውስጥ የሚጠበቅብንን ድርሻ ማበርከት።

*ተልዕኮ፦ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት በመንጌል ስርጭት መሳተፍ፤ የተጎዱትን፤ የተራቡና የተጠሙትን፤ የታረዙትንና የታመሙትን ለመርዳት የተልዕኮ (out reach) ፕሮግራሞችን ማመቻቸት።

የወንድሞች ኅብረት በየወሩ ወር በገባ በሦሥተኛው ቅዳሜ ከጠዋቱ ከ9፡00 እስከ 12፡00 ድረስ ይደረጋል።